በሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ 8 የማምረቻ ሼዶች ተገንብተው ለአገልግሎት ተዘጋጁ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ 8 የማምረቻ ሼዶች ተገንብተው ለአገልግሎት መዘጋጀታቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡
ኮርፖሬሽኑ ሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለኢትዮ-ጂቡቲ ወደብ ቅርበት ያለው ከመሆኑ አንጻር በፓርኩ መዋዕለ ነዋይ ማፍሰስ ጠቀሜታ እንዳለው አስታውቋል።
ልማቱ 98 በመቶ በተጠናቀቀው ፓርክ ውስጥ 8 የማምረቻ ሼዶች ተገንብተው ለአገልግሎት መዘጋጀታቸውን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የፓርኩ ግንባታ ከ2012 ዓ.ም ግንቦት ወር ጀምሮ በቻይናው ሲ ሲ ሲ ሲ ተቋራጭ እየተከናወነ ይገኛል።
የኢንዱስትሪ ፓርኩ በመንግስት እየለሙ ከሚገኙ ፓርኮች 13ኛው ነው።
በአፋር ክልል በሰመራ ከተማ የሚገኘው ይህ ፓርክ ጠቅላላ ስፋቱ 2 ሺህ ሄክታር ላይ ያረፈ ሲሆን÷ ፓርኩ ሲጠናቀቅ የሎጅስቲክ ፓርክ በመሆን ሌሎቹን ፓርኮች ያስተሳስራል ተብሎ ይጠበቃል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!