በምሥራቅ ወለጋ ዞን በጉቶ ጊዳ ወረዳ ለአሸባሪው ሸኔ ሊጓጓዝ የነበረ 1 ሺህ 103 ጥይት ተያዘ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉቶጊዳ ወረዳ ጋሪ ቀበሌ ለአሸባሪው ሸኔ ለማቀበል ሲጓጉዙ የነበረ 1 ሺህ 103 ጥይት በቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ገልጿል፡፡
የተያዙት 518 የብሬን እና 585 የክላሽ ጥይቶች በድምሩ 1 ሺህ 103 ጥይቶች መሆናቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
ጥይቶቹ የተያዙት በህዝብ ጥቆማና በጸጥታ አካላት ትብብር መሆኑም የወረዳው ፖሊስ ገልጿል፡፡
የወረዳው ፖሊስ ሃላፊ ዋና ሳጅን ከተማ ኦልጅራ እንደገለጹት÷ ጥይቱ ትናንት ከምሽቱ 3 ሠዓት ላይ ከነቀምቴ ከተማ ወደ ወላኔ ተራራ ለአሸባሪው ሸኔ ሊጓጓዙ ነው የተያዙት፡፡
በገላና ተስፋ