Fana: At a Speed of Life!

የመስኖ ዘርፍ ቴክኖሎጂ ለማሳደግ እና ክህሎት ያለው የሰው ሀይል ለማፍራት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር እና የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የመስኖ ዘርፍ ቴክኖሎጂ ለማሳደግ እና ክህሎት ያለው የሰው ሀይል ለማፍራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ እና የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ፈርመዋል፡፡
በመስኖ ዘርፍ ብዙ የሰው ኃይል የሚሰማራ መሆኑን የገለጹት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ÷ የሚሳተፈው የሰው ኃይል ስለዘርፉ ቴክኖሎጂ ግንዛቤ ያለውና ጤናው የተጠበቀ እንዲሆን እንዲሁም የውሃ መሰረተ ልማትን በአግባቡ ሥራ ላይ ለማዋል መግባቢያ ሰነዱ መፈረሙን ተናግረዋል፡፡
የመስኖ ዘርፍ ቴክኖሎጂ ለማሳደግ፣ ክህሎት ያለው የሰው ሀይል ለማፍራት፣ በመስኩ ለሚሰማሩ ዜጎች የሙያ ደህንነት ለመፍጠር የስምምነት ሰነድ መፈረሙን የገለጹት ደግሞ የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ናቸው፡፡
የተናበበና የተቀናጀ የአሠራር ሥዓርት በመዘርጋት አላስፈላጊ የሆነ የሀብት እና የጊዜ ብክነትን በማስቀረት ሀገር ወዳድ፣ ብቁ፣ ተወዳዳሪና በሙያው የሚተማመን የሰው ኃይል በማፍራት በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር በሚተገበሩ ፕሮግራሞች ላይ እንዲሳተፉ ለማስቻል እንደሚያግዝ መገለፁን ከመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የፕሮጀክት አፈጻጸም ውጤታማነትን በማሳደግ ህብረተሰቡ ከዘርፉ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆንና ለስራ ፈላጊ ዜጎች የስራ ዕድል በመፍጠር ለሃገሪቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያ ዕድገት ከዘርፉ የሚጠበቅበትን ሚና እንዲወጣ ለማድረግ እንደሚያስችልም በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.