Fana: At a Speed of Life!

ሱዳናውያን በአገሪቱ መንግስት ላይ የሚያደርጉትን ተቃውሞ ቀጥለዋል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳናውያን በወታደራዊው መንግስት ላይ የሚያደርጉትን ሰላማዊ ሰልፍ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡
በሱዳን ወታደራዊ መንግስት እና የሲቪል አስተዳደር የነበረው ውጥረት ባለመርገቡ ባለፈው ጥቅምት ወር የሱዳን ወታደራዊ ኃይል መፈንቅለ መንግስት አካሂዷል፡፡
ይህንን ያልተቀበሉት ሱዳናውያን ላለፉት 5 ወራት ተቃውሟቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ሲገልፁ የቆዩ ሲሆን፥ በርካቶችም በፀጥታ አካላት ለጉዳት እና ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡
በትላንትናው እለትም በሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ወታደራዊ መንግስቱን በመቃወም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡
በተካሄዱ ሰልፎች የሱዳን የፀጥታ ኃይሎች አስለቃሽ ጭስ በመልቀቅ ሰልፉን ለመበተን ሙከራ ሲያደርጉ እንደነበር አፍሪካ ኒውስ ዘግቧል፡፡
ባለፈው ጥቅምት ወር የተካሄደው የጄኔራል አብዱልፈታህ አል ቡርሀን መፈንቅለ መንግስት አገሪቱን ለከፋ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ዳርጓታል ነው የተባለው።
በሀገሪቱ ያለው የዋጋ ግሽበት ከ250 በመቶ በላይ የደረሰ ሲሆን፥ ከመፈንቅለ መንግስቱ ወዲህ የዳቦ፣ የመብራት እና የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩም ተመላክቷል።
እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቅርብ ጊዜ ሪፖርት፥ ከ45 ሚሊየን ሱዳናውያን ግማሽ ያህሉ የምግብ ዋስትናቸው ያልተረጋገጠ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.