አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዶክተር አኔት ዌበር ጋር ተወያዩ።
በውይይታቸው በወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ እና በአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውን አምባሳደር ታዬ በማህባረዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
ከዚህ ባለፈም የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ እንዲሆን በተወሰደው የተኩስ ማቆም ውሳኔ ዙሪያም ምክክር አድርገዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!