Fana: At a Speed of Life!

ቤተክርስቲያኗ በሰሜን ሸዋ ዞን በግጭቱ ጉዳት ለደረሰባቸውን ወገኖች ማቋቋሚያ የ58 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተከሰተው ግጭት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች መልሶ ለማቋቋም የ58 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማድረጓን የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት አስታወቀች፡፡
የቤተ ክርስቲያኗ የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከት የማኅበራዊ እና ልማት ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አማን ደግፍ÷ በሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ በመገኘት ድጋፉን ለነዋሪዎች አስረክበዋል፡፡
የሰብዓዊ ድጋፉን ለማጠናከም አጋር የልማት ተቋማትን በማስተባበር ከ58 ሚሊየን ብር በላይ አሰባስበን እየተንቀሳቀስን ነው ብለዋል፡፡
ድጋፉ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተፈጸመው ጥቃት ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ሲሆን ÷በስድሥት ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ላይ የሚተገበር መሆኑን ሃላፊው ገልጸዋል፡፡
ድጋፉ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፣ የንፅህና መጠበቂያ እንዲሁም ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ አቅርቦቶችን ያካተተ ነው ተብሏል።
በድጋፉ ቀወት፣ ኤፍራታና ግድም እና አንጾኪያ ገምዛ ወረዳዎች እንዲሁም ሸዋሮቢት፣ አጣዬ እና ደብረ ብርሃን የድጋፉ ተጠቃሚ ከሆኑ ከተሞች መካከል መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያኗ በማኅበራዊ ልማቶች ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች እንደሆነና መሰል ድጋፎች ማድረጓንም እንደምትቀጥል ተመላክቷል፡፡
በሰላም አሰፋ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.