Fana: At a Speed of Life!

የሩሲያ- ዩክሬን ግጭት ዓለምን ወደ አዲስ “የቀዝቃዛ ጦርነት ዘመን” እየወሰደ ነው ስትል ቱርክ አስጠነቀቀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያ- ዩክሬን ግጭት ዓለምን ወደ አዲስ “የቀዝቃዛ ጦርነት ዘመን” እየወሰደ ነው ስትል ቱርክ አስጠነቀቀች።
የቱርክ ፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ቃል አቀባይ ኢብራሄም ካሊን እንደገለፁት፥ ዓለምን ወደ አዲስ የቀዝቃዛ ጦርነት እየወሰደ ነው ካሉት የዩክሬን እና ሩሲያ ግጭት ተፅእኖ ለመውጣት አስርት ዓመታትን ይወስዳል።
ቃል አቀባዩ ሀያላን ሀገራት በዓለም የሀይል ሚዛን ብልጫ ለመውሰድ እና የአጭር ጊዜ ጥቅምን በማስላት መፋጠጣቸው የዩክሬን ቀውስን እያባባሰው መሆኑን ተናግረዋል።
ይህም በመካከለኛና በረዥም ጊዜ ውስጥ የሚታይ ስትራቴጂያዊ እና የሰብዓዊ ጉዳት እንደሚያደርስ ነው ያስረዱት።
አክለውም ሩሲያ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ ቱርክ የሰላም ንግግሮች እንዲደረግ ግፊት ስታደርግ መቆየቷን እና በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረውን ግጭት ለማብረድ አሸማጋይ ሆና መቆየቷን ጠቅሰዋል፡፡
እንደ አሜሪካ እና ምዕራባውያን ሩሲያ ላይ ማዕቀብ ከመጣል ይልቅ በገለልተኝነት ከሁለቱም ወገኖች ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን መቀጠሏንም ገልፀዋል፡፡
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በሩሲያ እና በምዕራቡ ዓለም መካከል ያለው ውጥረት እየተባባሰ መምጣቱን ተከትሎ አለማቀፉ ማህበረሰብ አዲስ የአለም ቀዝቃዛ ጦርነት ስጋት ውስጥ መግባቱን የቲ አር ቲ ዘገባ አመልክቷል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.