Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ለዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ ለዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው የመድኃኒት፣ የህክምና እና የቢሮ ቁሳቁስ ድጋፍ አስረከበ፡፡
የኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ የመድኃኒት አቅርቦትና የፋርማሲ አገልግሎት ባለሙያ አቶ አለሙ ታፈሰ÷ ድጋፉ በጦርነቱ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የዋግ ኽምራ ዞን ጤና ተቋማት የሚውል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የተደረገው ድጋፍ የተለያዩ መድኃኒቶች፣ የቀዶ ጥገና መስሪያ ቴብል፣ ለቀዶ ጥገና አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች ማፅጃ ፣ መካኒካል ቬንትሌተር፣ የሰመመን ህክምና መስጫ መሳሪያ፣ የተሻሻሉ አልትራ ሳውንዶች፣ የኦክስጅን መስጫ መሳሪያዎች እና ሌሎችም ቁሳቁስ ያካተተ ሲሆን÷ አጠቃላይ ግምቱም ከ20 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ መሆኑን አቶ አለሙ አብራርተዋል፡፡
የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ ዶክተር ኪዳት አየለ በበኩላቸው÷ በጦርነቱ ምክንያት በርካታ የጤና ተቋማት በመውደማቸው ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ከዋግ ኽምራ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.