Fana: At a Speed of Life!

በጎሮ ጉዱ ወረዳ ሲካሄድ የቆየው የኦሮሚያ -ሶማሌ ወንድማማችነት መድረክ በስኬት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ወንድማማችነት ለዘላቂ ሰላም” በሚል መሪ ቃል በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ጎሮ ጉዱ ወረዳ ሲካሄድ የቆየው የኦሮሚያ-ሶማሌ ወንድማማችነት መድረክ በስኬት ተጠናቀቀ፡፡
የመድረኩ ዋና ዓላማ÷ የሁለቱን ክልሎች ሕዝብ የእርስ በርስ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር መሆኑ ተመላክቷል፡፡
በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በግጦሽ እና በውኃ ምክንያት አልፎ አልፎ ሲከሰት የነበረውን ግጭት ማስቀረት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ነው መድረኩ የተጠናቀቀው፡፡
በመድረኩ ላይ አባገዳዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የጸጥታ አካላት እና በየደረጃው ያሉ የመንግሥት ሥራ አመራሮች መገኘታቸውን ከምሥራቅ ሐረርጌ ዞን ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.