Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ሸዋ ዞን ጉዳት ለደረሰባቸው የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከ5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ደብረሲና፣ ይፋት፣ አጣዬ፣ መሐልሜዳና ሞላሌ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ከ5 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የአይነት ድጋፍ ተደረገ።
በአዲስ አበባ ስራና ስልጠና ቢሮ የአራዳና ልደታ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጆች 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርጉ÷ በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙ 12 ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ደግሞ 3 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚጠጋ ድጋፍ አድርገዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ወልደ አማኑኤል÷ በአጠቃላይ በዞኑ በሚገኙ ኮሌጆች 80 ሚሊየን ብር ጉዳት መድረሱን አስታውሰው÷ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡
ከጉዳቱ አንጻር የተደረጉ ድጋፎች በቂ ባለመሆናቸው ሌሎች ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሳምራዊት የስጋት
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.