Fana: At a Speed of Life!

23 የኢራን ፓርላማ አባላት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣2012 (ኤፍ ቢ ሲ ) በኢራን 23  የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተሰምቷል።

የምክር ቤቱ ምክትል ሊቀ መንበር ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥ፓርላማው ካሉት 290 አባላት ውስጥ 23 የሚሆኑት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ተናግረዋል።

አባላቱ በቫይረሱ የተያዙትም ለስራ ጉዳይ በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ ከሰዎች ጋር በነበራቸው ግንኙነት ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ሃላፊው ጠቁመዋል።

በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ መስፋፋቱን ተከትሎ ፓርላማው ሲያካሂደው የነበረውን ስብሰባ ማራዘሙም ተመላክቷል።

በኢራን በአሁኑ ወቅት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 77 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ 2 ሺህ 336 የሚሆኑ ዜጎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል።

ይህን ተከትሎም ኢራን ከቻይና ቀጥላ ቫይረሱ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰባት ሀገር መሆኗ ነው የተገለጸው።

ምንጭ፥ https://www.middleeasteye.net

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.