Fana: At a Speed of Life!

ምክር ቤቱ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ለዝርዝር ዕይታ መራ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አይቶ ለዝርዝር ዕይታ መራ።
ምክር ቤቱ ባካሄደው 8ኛ መደበኛ ስብሰባ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት እንደገና ለማቋቋም የወጣውን አዋጅ ለማሻሻል መርምሮ ለዝርዝር ዕይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት ላይ ተወያይቷል።
በምክር ቤቱ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ ረቂቅ አዋጁን በተመለከተ ባቀረቡት መግለጫ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የተቀመጠውን የሪፎርም አቅጣጫ ለማሳካት ጥናት ሲያካሂድ መቆየቱን ገልጸው÷ ተቋሙ ተልዕኮውን በብቃት መወጣት እንዲችል የአዋጅ ማሻሻያ መቅረቡን ተናግረዋል።
በአገሪቱ ላይ የሚፈጸመውን ጦርነት የመመከት ሂደት በአግባቡ ካልተመራ ብሔራዊ ደህንነትና ጥቅምን ለአደጋ ሊያጋልጥ የሚችል በመሆኑ ÷ የሚቃጣውን የስነ ልቦና ጦርነትን ለመመከት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ተግባራትን በበላይነት የሚመራና የሚያስተባብር ተቋም እንዲሆን በማስፈለጉ እነዚህን ተግባራት የሚያመላክት ድንጋጌ እንዲካተት ተደርጓ ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የምክር ቤቱ አባላት በረቂቁ ላይ አስተያየት ከሰጡ በኋላ ለዝርዝር እይታ ረቂቅ አዋጅ 7/2014 ሆኖ በዋናነት ለህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተባባሪነት ደግሞ ለውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች በሙሉ ድምጽ ተመርቷል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.