ጣሊያን ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ትምህርት ቤቶችን ልትዘጋ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጣሊያን መንግስት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ትምህርት ቤቶችን እና ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ሊዘጋ ነው።
ትምህርት ቤቶቹ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ በሚል እንደሚዘጉ የሃገሪቱን ባለስልጣናት ዋቢ ያደረገው የሬውተርስ ዘገባ ያመላክታል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ለሁለት ሳምንታት ይዘጋሉ ነው የተባለው፤ አሁን ላይ የቫይረሱ ስርጭት ከፍተኛ በሆነባቸው የሃገሪቱ ሰሜናዊ አካባቢዎች የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል።
በጣሊያን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ይገኛል።
እስካሁን ባለው መረጃም 79 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ ከ2 ሺህ 500 በላይ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል።
ምንጭ፦ ሬውተርስ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision