ቱርክ በድንበር አካባቢ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ ልታግድ ነው
አዲስ አበባ፣የካቲት 26፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ)ቱርክ ከግሪክ ጋር በምትዋሰንባቸው ድንበር አካባቢ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ እየሰራች መሆኑን አስታውቃለች።
ግሪክ ወደ አውሮፓ ሀገራት ለመግባት ተስፋ የሚያደርጉ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን እንዳይገቡ እየሰራች ነው ተብሏል፡፡
ለዚህም ስደተኞቹ ድንበሯን አቋርጠው እንዳይገቡና ወደ ቱርክ ለመመለስ የግሪክ ድንበር ጠባቂዎች የአስለቃሽ ጋዝ መጠቀማቸውም ነው የሚነገረው፡፡
ቱርክ ሁሳኔውን ያሳለፈችውም ግሪክ ስደተኞች ድንበሯን አቋርጠው እንዳይገቡ ወደ ቱርክ የመመለስ ስራ እያከናወነች መሆኑን ተከትሎ ነው ተብሏል።
የቱርክን ውሳኔን ተከትሎ የአውሮፓ ህብረት የቱርክን ፖሊሲን አውግዟል ነው የተባለው፡፡
የግሪክ መንግሥት በበኩሉ ቅዳሜ ማለዳ ላይ ጀምሮ በህገ-ወጥ መንገድ ሊገቡ የነበሩ 34 ሺህ 778 ሰዎች መከልከሉንና 244 ሰዎችን ደግሞ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል፡፡
ድንበሩ ላይ ካሉ ስደተኞች መካከል ሶርያውያን፣ አፍጋኒስታን፣ ፓኪስታን እና ምእራብ አፍሪካውያን እንደሚገኙበትም ነው የተጠቆመው፡፡
ምንጭ፡-ቢ.ቢ.ሲ