1ሺህ 38 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ የመመለስ ሥራ 1ሺህ 38 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡
ከተመለሱት ዜጎች መካከልም÷ 158 ሕጻናትና 880 ወንዶች መሆናቸውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት እንዲሄዱ መደረጉም ተገልጿል፡፡
እስካሁን ድረስ በተከናወነ ዜጎችን የመመለስ ሥራ ከ31 ሺህ 236 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉም ተገልጿል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!