Fana: At a Speed of Life!

የሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሳካ የግሉ ዘርፍ ሚና ከፍተኛ ነው – አቶ ንጉሡ ጥላሁን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የተቋቋመለት የሥራ ዕድል ፈጠራ ተልዕኮ እንዲሳካ የግሉ ዘርፍ ሚና ከፍተኛ ነው ሲሉ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ተናገሩ፡፡
የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ከሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በጋራ ያዘጋጁት ጥቃቅን እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች የተሳተፉበት 12ኛው የኢትዮ ቻምበር ዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒት ተጠናቋል።
በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት አቶ ንጉሡ ጥላሁን÷ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የተቋቋመለት የሥራ ዕድል ፈጠራ ተልዕኮ እንዲሳካ የግሉ ዘርፍ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክርቤት የግሉን ዘርፍ ያሰባሰበ በመሆኑ÷ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በዓለም አቀፍ የንግድ ትርዒትም ሆነ በሌሎች ትልልቅ ጉዳዮች ላይ ተባብሮ እንደሚሠራ ተናግረዋል፡፡
“የኢትዮጵያን ይግዙ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ “በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የንግድ ትርዒት ላይ ከ250 በላይ አምራች ኢንተርፕራይዞች እና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የተሳተፉ ሲሆን÷ ከእነዚህ መካከልም በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ድጋፍ ከ60 በላይ ሞዴል ኢንተርፕራይዞች መሳተፋቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የዓለም ዓቀፉ የንግድ ትርዒት አካል የሆነው ከ50 በላይ ከንቲባዎች የተሳተፉበት የግሉ ዘርፍ እና ከንቲባዎች ምክክር መድረክ የተካሄደ ሲሆን÷ በዚህም የአቻ ለአቻ የንግድ መድረክ፣ የፓናል ውይይቶች እንዲሁም ሥራና ሰራተኞች የተገናኙበት መድረክ እንደነበር ተመላክቷል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.