Fana: At a Speed of Life!

10 የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት መስጫ ማዕከላት መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በ91 ሚሊየን ብር 10 የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱን የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ከ8 የህብረት ስራ ማህበራትና ከሁለት ስራ ፈጣሪ ኤጀንሲዎች ጋር ተፈራርሞታል።

ማዕከላቱ በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ እና ትግራይ ክልሎች የሚገነቡ ሲሆን፥ የማዕከላቱ ግንባታ 70 በመቶ ወጪ በኤጀንሲው የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል።

ቀሪው 30 በመቶ ደግሞ በህብረት ስራ ማህበራቱ የሚሸፈን ይሆናል።

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ዋና ስራ አስፈጻሚ ካሊድ ቦምባ፥ የግብርና ሜካናይዜሽን ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም የአነስተኛ ማሳ ተጠቃሚ አርሶ አደሮችን ህይዎት ለማሻሻል ይረዳልም ነው ያሉት።

ማዕከላቱ ከመሬት ማለስለስ እስከ ምርት መሰብሰብና ማጓጓዝ ድረስ ባለው ሂደት ለአርሶ አደሮች እገዛ በማድረግ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ይረዳሉ ነው የተባለው።

አገልግሎቱ የግብርና ሚኒስቴር በዴንማርክ እና ኔዘርላንድስ መንግስት ድጋፍ ለሶስት አመታት የሚተገበረው የሙከራ ፕሮጀክት መሆኑም በፊርማ ስነ ስርአቱ ወቅት ተገልጿል።

የማዕከላቱ ውጤታማነት እየታየም ፕሮጀክቱ በሌሎች የሃገሪቱ አካባቢዎች በቀጣይነት እንደሚተገበር ኤጀንሲው ለጣቢያችን የላከው መግለጫ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.