Fana: At a Speed of Life!

ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በኢትዮጵያ ከዴንማርክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በኢትዮጵያ የዴንማርክ አምባሳደር ኪራ ስሚዝን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
 
በውይይታቸውም የዴንማርክ መንግሥት በሲዳማ ክልል በንፁህ መጠጥ ውሃ ልማት አቅርቦት ላይ ከክልሉ ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳለው አምባሳደሯ ተናግረዋል፡፡
 
በዚህም የዴንማርክ መንግሥት በሲዳማ ክልል ሃዋሳ ከተማ እና በተለያዩ ወረዳዎች በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና በዘርፉ በአቅም ግንባታ ሥራዎች ላይ መስራት እንደሚፈልግ ጠቁመዋል።
 
አቶ ደስታ ሌዳሞ በበኩላቸው÷የዴንማርክ መንግሥት በክልሉ ለሚከናወነው የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሥራ ለሚያደርገው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
የክልሉ መንግሥት ለሥራው የሚያስፈልጉ ድጋፎችን እንደሚያደርግ ማረጋገጣቸውን ከርዕሰ መስተዳደሩ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.