Fana: At a Speed of Life!

በአምባሰል ወረዳ ራስ ጠቆሮ ጥብቅ ደን ላይ የእሳት አደጋ ተከሰተ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል ወረዳ 8 ሄክታር የቆዳ ስፋት ባለው ራስ ጠቆሮ እየተባለ በሚጠራው ጥብቅ ደን ላይ የእሳት አደጋ መከሰቱ ተገለፀ፡፡

የእሳት አደጋው ከሰኔ 6 ቀን 2014ዓ.ም ሌሊት ጀምሮ የተከሰተ መሆኑ እና እስካሁን ድረስ መቆጣጠር አለመቻሉ ተገልጿል፡፡

ከመልክዓ ምድራዊ አቀማመጡ አመቺ አለመሆንና በደኑ ውስጥ ተቀጣጣይ ሳር ከመብዛቱ ጋር ተያይዞም የእሳት አደጋውን ለማጥፋት የሚደረገውን ጥረት ሥራውን ፈታኝ እንዳደረገው ተጠቁሟል።

የአደጋው መንስኤ በተመለከተም እሳቱ ከግለሰብ ማሳ ተነስቶ ወደ ደኑ እንደተዛመተ ታውቋል፡፡

የአምባሰል ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ ተጠሪ ጽህፈት ቤት ተወካይ ኃላፊ ወይዘሮ ዚነት ሙሃመድ ÷ የደኑ የቆዳ ስፋት 8 ሄክታር መሆኑን ገልፀው እሳቱ የተነሳው በምስራቅ አቅጣጫ ዲሽቅ ተራራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ስፍራው እንዳመራ መናገራቸውን ከደቡብ ወሎ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በጥብቅ ደኑ ወይራ፣ ጥድ፣ ኮሶ፣ ዝግባና ሌሎች የደን ሐብቶች እንዲሁም ነብርን ጨምሮ ሌሎች የተለያዩ አጥቢ እንስሳትና አዕዋፋት እንደሚገኙ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.