በአማራ ክልል ባለፉት 11 ወራት ከ137 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷል
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ባለፉት 11 ወራት ውስጥ ከ137 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መሰጠቱ ተገለጸ፡፡
በክልሉ በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በማዕድንና ሌሎች ዘርፎች ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭና ምቹ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኢንቨስት ለማድርግ የሚመጡ ባለሃብቶች ፍሰት መሻሻል አሳይቷል ተብሏል፡፡
በዚህም ባለፉት 11 ወራት ውስጥ 137 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ያስመዘገቡና በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ ሲገቡ ከ457 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ሊፈጥሩ የሚችሉ 2 ሺህ 321 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ክልሉ እነዚህ ባለሃብቶች ባቀረቡት ፕሮጀክት መሰረት ፈጥነው ወደ ስራ በመግባት ለዜጎች የስራ እድል እንዲፈጥሩና የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት የሚያስችል ምርት እንዲያመርቱ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል መባሉን ከአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!