አሸባሪው ሸኔ እየተወሰደበት ያለውን እርምጃ መቋቋም ሲያቅተው በንጹሃን ላይ ጥቃት እያደረሰ ነው – የኦሮሚያ ክልል መንግስት
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የሸኔ ቡድን በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ባደረሰው ጥቃት በንጹሃን እና በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡
አሸባሪው የሸኔ ቡድን መንግሥት እየወሰደበት ያለውን እርምጃ መቋቋም ሲያቅተው÷ በንጹሃን ላይ ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት ማድረሱን የኦሮሚያ ክልል አስታውቋል፡፡
የፌደራል እና የክልሉ የጸጥታ አካላት በአሸባሪው ሸኔ ላይ የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው እንደሚቀጥሉም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያወጣው መግለጫ አመላክቷል፡፡
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥትም በንጹሃን ላይ በደረሰው ጥቃት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!