ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በበርካታ ንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ድርጊት አወገዙ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በበርካታ ንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ድርጊት አወገዙ፡፡
ፕሬዚዳንቷ፥ ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለን አግኝተው ስለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ሁኔታ በተለይም ባለፉት ቀናት ሴቶችና ህጻናትን ጨምሮ በበርካታ ንጹሃን ዜጎች ላይ ስለተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡
አሰቃቂ ግድያውን በጽኑ እንደሚያወግዙም ነው ያስታወቁት፡፡
ፕሬዚዳንቷ እንዳሉትም፥ በየትም ቦታ የዜጎች ሕይወት ውድነቱና ክብሩ መሸርሸር የለበትም፡፡
አክለውም ፥ “ሞትን ከተለማመድነው ከግድያ በኃላ ከማውገዝና የሃዘን መግለጫ ከማውጣት አዙሪት አናልፍም፤ ከዚያ በላይ መሄድ ይኖርብናልም” ማለታቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!