Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ከንቲባው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የነዋሪዎችን ቤት እድሳት አስጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ዓባይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 የሚገኙ ነዋሪዎችን የቤት እድሳት አስጀመሩ፡፡
አዲሱ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኙ ስድስት መኖሪያ ቤቶችን አፍርሶ እንደገና የሚያስገነባው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምግብ፣ መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መሆኑ ተገልጿል፡፡
የተቋሙን ደንበኞች በማስተባበር በተገኘ በጀት ግንባታውን ለመገንባት ተስማምተው መረከባቸውንም የባለስልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር ወይዘሮ ትዕግስት በዳዳ ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ዓባይ የቤት እድሳቱን ባስጀመሩበት ወቅት እንደገለጹት÷ የአቅመ ደካማ ቤቶችን በጋራና በትብብር ለማደስ የምናደርገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ ሽታዬ መሀመድ በበኩላቸው÷ በተያዘው ክረምት ከ300 በላይ ቤቶችን ለማደስ ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ ነው ማለታቸውን የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል፡፡
ግንባታውን የተረከቡ አካላትም በተቻለ መጠን በአጭር ጊዜ አጠናቀው ለነዋሪዎቹ እንዲያስረክቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.