አቶ ብናልፍ አንዷለም በሰላም ግንባታ ሂደት ላይ ከቀጠናው የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም በሰላም ግንባታ ሂደት ላይ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና ኤርትራ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን ጋር ተወያዩ፡፡
አቶ ብናልፍ ከኦስማን ዲዮን ጋር በኢትዮጵያ በመከናወን ላይ የሚገኙ የዘላቂ ሰላም ግንባታ ተግባራትን በሚመለከት ተወያይተዋል፡፡
በሰላም ግንባታ ሂደት ላይም በጥልቀት የተወያዩ ሲሆን፥ የዓለም ባንክ በዘላቂ ሰላም ግንባታ ስራዎች ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በአጋርነትና በትብብር ለመስራት ያለውን ፍላጎት ኦስማኒ ዲዮን ገልጸዋል፡፡
በቀጣይም በኢትዮጵያ መንግስት የተያዙ ፕጀክቶችን እና ፕሮግራሞችን በፋይናንስና በቴክኒክ ለመደገፍና ከኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ጎን ለመቆም የዓለም ባንክ ዝግጁ ነው ማለታቸውን ከሰላም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
በተመሳሳይ የሥራ ሀላፊዎቹ በሰላም ሚኒስቴር በዘመናዊ መልክ በመደራጀት ላይ የሚገኘውን የቅድመ ግጭት መከታተያ ክፍል ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!