በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ መከፈቱ የሁለቱን አገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ያጠናክራል ተባለ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በፓኪስታን እስላማባድ ኤምባሲ እንዲከፈት መድረጉ የሁለቱን አገራት የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ይበልጥ እንደሚያጠናክረው የአገሪቱ ባለሥልጣን ገለጹ።
የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ጀማል በከር ዛሬ በአገሪቱ መዲና እስላማባድ ገብተዋል፡፡
የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ በካሄደው ሪፎርም መሰረት የአገራችን ብሔራዊ ጥቅምና ክብር ለማስጠበቅ በፓኪስታን እስላማባድ ኤምባሲ እንዲከፈት በወሰነው መሰረት በፓክስታን የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ጀማል በከር የተጣለባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዛሬ በአመዲናዋ መግባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ አምባሳደር ጀማል በከር በፓክስተን ቤናዝር ቡቶ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የፓክስታን ምክትል የፕሮቶኮል ዋና ዳይሬክቴር አዴል አህመድ አቀባበልና መስተንግዶ አድርገውላቸዋል፡፡
አምባሳደር ጀማል በከር በበኩላቸው፥ የተደረገላቸውን መልካም መስተንግዶና አቃባበል አድንቀው በቀጣይ በአጭር ጊዜ ኤምባሲውን አደረጅተው ወደ ተግባር ለመግባት የፓክስታን መንግስት ድጋፍ እንደማይለያቸው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡፡
የፓኪስታን የፕሮቶኮል ምክትል ዋና ዳይሬክተር የኢፌዴሪ መንግስት በፓክስታን ኤምባሲ መክፈቱን አድንቀው፥ በቀጣይም የሁሉቱ አገራት የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ይበልጥ እንዲጠናከር ኤምባሲው በአፈጣኝ ወደ ስራ እንዲገባ መንግስታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ለአምባሳደሩ አረጋግጠውላቸዋል፡፡
ለአምባሳደሩ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸውም ልባዊ ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል።
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!