አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብርን አስጀመሩ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ጋር በመሆን በጅግጅጋ ከተማ የክረምት የበጎ ፈቃድ መርሐ ግብር አስጀምረዋል።
በጅግጅጋ ከተማ ዛሬ በተጀመረው የክረምት የበጎ ፈቃድ ስራ 30 የአቅመ ደካማ ዜጎች ቤት እድሳት መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል።
በተጨማሪም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ የተከናወነ ሲሆን÷ በዚሁ ወቅት በሚኒስትር ማዕረግ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተስፋዬ በልጅጌ እንደገለጹት÷ የዓለም አየር ንብረት ለውጥ መዛባት የተከሰተው በደን መመናመን እንደመሆኑ የአረንጓዴ አሻራ መካሄዱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።
በተለይም ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ሚናው የጎላ ነው ብለዋል።
እንደ ሶማሌ ክልል ባሉ ድርቅ የተከሰተባቸው አካባቢዎች እንዲያገግሙ ሚናው የጎላ መሆኑን ጠቁመው÷ መርሐ ግብሩ እርስ በእርስ የመረዳዳት ባህልን የሚያጎለብት መሆኑንም ገልፀዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ ተቋማት አባላትና አመራሮች ተሳትፈዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-