በኦሮሚያ ክልል በአንድ ጀምበር ከ448 ነጥብ 6 ሚሊየን በላይ ችግኝ ተተከለ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በአንድ ጀምበር በተካሄደ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 448 ሚሊየን 622 ሺህ 319 ችግኞች መትከል መቻሉን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ፡፡፡
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የዘንድሮውን ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በምሥራቅ ሸዋ ዞን ሉሜ ወረዳ በዛሬው ዕለት አስጀምረዋል፡፡
የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ በክልሉ በሚገኙ 20 ዞኖች እና 19 ከተሞች ነው ሲከናወን የዋለው፡፡
በአንድ ጀምበር በተካሄደ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብርም 400 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ 448 ሚሊየን 622 ሺህ 319 ችግኞች መትከል መቻሉን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታውቋል፡፡
በሉሚ ወረዳ በተካሄደው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ 300 ችግኞችን መትከላቸው ተጠቁሟል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!