Fana: At a Speed of Life!

በአቶ አሻድሊ ሀሰን የተመራ ልዑክ በመተከል ዞን የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አሻድሊ ሀሰን የተመራ የክልልና የዞን አመራሮች ልዑክ በመተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ በኩታ ገጠም የለማ የበቆሎ ሰብልን ጎበኘ።
ከጉብኝቱ በተጨማሪ ከማንዱራ ወረዳ ፎቶ ማንጃሪ ቀበሌ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በቀጠናው እየተካሄደ ያለውን ሕግ የማስከበር ተግባር ተከትሎ የተገኘውን ሰላም በዘላቂነት በመያዝ አርሶ አደሮቹ ወደ መደበኛ ሥራቸው እንዲገቡ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡
በአካባቢው በተከሰተው አለመረጋጋት ተቋርጦ የነበረውን የግብርና ሥራ አጠናክሮ ለማስቀጠል÷ ከአሁን በፊት ከገቡት በተጨማሪ 10 የእርሻ ትራክተሮች ለዞኑ እንደሚሰጡም ተናግረዋል።
የሕዝቦችን አንድነት የማይፈልጉ ኃይሎችን በጋራ በመታገል የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም አሳስበዋል።
ባለፈው ዓመት በተፈጠረው ግጭት የወደሙ መሰረተ ልማቶችን የክልሉ መንግሥት መልሶ ለመገንባት በትኩረት እየሠራ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
በወረዳው በተያዘው ዓመት 48 ሺህ ሔክታር በዘር ለመሸፈን ታቅዶ እስካሁን 25 ሺህ 500 ሔክታር በዘር መሸፈኑን የመተከል ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
የውይይቱ ተሳታፊ አርሶ አደሮች በበኩላቸው÷ በተገኘው አንጻራዊ ሰላም ወደ መደበኛ የግብርና ሥራቸው በመሰማራት የበቆሎ ሰብልን በኩታ ገጠም እያለሙ መሆኑን ገልጸው÷ መንግስት የጀመረውን ሕግ የማስከበር ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.