Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስ አለም አቀፍ ወረርሽኝ ሆኖ በአለም ጤና ድርጅት ታወጀ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 2፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኮሮና ቫይረስ አለም አቀፍ ወረርሽኝ መሆኑን የአለም ጤና ድርጅት በዛሬው ዕለት አወጀ።
 
የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የኮሮና ቫይረስ ከቻይና ውጪ ባለፉት ሁለት ሳምንታት በ13 እጥፍ ከፍ ማለቱን ተናግረዋል።
 
ዶክተር ቴድሮስ ቫይረሱን ለመከላከል የሚታየው የተግባር ውስንነት በእጅጉ እንደሚያሳስባቸው ገልፀዋል።
 
ቫይረሱ አለም አቀፍ ወረርሽኝ ነው ማለት ድርጅቱ ሀገራት ሊሰሩት ይገባል ብሎ ያቀረበው ምክረ ሀሳብ ይቀየራል ማለት አይደለም ብለዋል።
 
ዶክተር ቴድሮስ ሀገራት ቫይረሱን ለመከላከል አስቸኳይ እና ከበድ ያለ እርምጃ በመውሰድ ሂደቱን ሊቀይሩ ይገባል ነው ያሉት።
 
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን በተመሳሳይ ወቅት በበርካታ ሀገራት የተሰራጨ በሽታ ሊሆን ችሏል።
 
የአለም ጤና ድርጅት 114 ሀገራት 118 ሺህ ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸውን እና 4 ሺህ 291 ሰዎች ደግሞ መሞታቸውን አስታውቋል።
 
ምንጭ፡- ቢቢሲ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.