Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በአውሮፓ ሃገራት ላይ የጉዞ እገዳ ጣሉ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በአውሮፓ ሃገራት ላይ አዳዲስ የጉዞ እገዳዎችን ጥለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ከ26 የአውሮፓ ሃገራት ወደ አሜሪካ የሚደረጉ ጉዞዎችን ለ30 ቀናት ማገዳቸውንም አስታውቀዋል።

እገዳው ከነገ እኩለ ሌሊት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፥ አሜሪካውያን ዜጎችን አያካትትም ተብሏል።

ትራምፕ እገዳውን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ “ጠንካራ ግን አስፈላጊ” የሆኑ የጉዞ ገደቦች በእንግሊዝ ላይ አይተገበሩም ብለዋል።

አሁን ላይ በአሜሪካ 1 ሺ 135 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን፥ 38 ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል።

መነሻውን ቻይና ውሃን ከተማ ያደረገው ኮሮና ቫይረስ አድማሱን እያሰፋ በርካታ ሃገራትን አዳርሷል።

የዓለም ጤና ድርጅትም ቫይረሱ ዓለም አቀፍ የጤና ወረርሽኝ መሆኑን አውጇል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.