Fana: At a Speed of Life!

አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ዓላማውን በማስተዋወቅ ሂደት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ ትብብርና ተቀባይነት ማግኘቱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዓላማውን በማስተዋወቅ ሂደት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ ትብብርና ተቀባይነት ማግኘቱን የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ገለጹ።

የምክክር ኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረሥላሴ÷ ኮሚሽኑ ዓላማዎቹንና ሥራዎቹን በጥልቀት ለማስተዋወቅ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመንቀሳቀስ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ እስካሁን ከፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፣ ከሲቪል ማህበራት፣ ከሃይማኖት አባቶችና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመገናኘት ዓላማውን አስተዋውቋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ከፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር በተደረገው ውይይትም÷ አብዛኞቹ ምክክሩ ውጤታማ እንዲሆን አብረው ለመሥራት እና ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል ነው ያሉት።

ለሀገራዊ ምክክሩ የበለጠ ጊዜ የሚወስደው የዝግጅት ምዕራፉ መሆኑን ጠቁመው÷ ውጤታማ እንዲሆን ከሁሉም አካላት ጋር እየተሰራ  ነው ብለዋል፡፡

ለአገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት መላው ኢትዮጵያውያን ኮሚሽኑን በመተባበርና በማገዝ እያሳዩት ያለውን መልካምሥራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ምክትል ዋና ኮሚሽነሯ ጠይቀዋል።

በኢትዮጵያ መሰረታዊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በመመካከር የጋራ መግባባት ለመፍጠር አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ተቋቁሞ ሥራ መጀመሩ ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግና

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.