ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ የምታገኘው ገቢ ለንግድ የምታወጣውን ወጪ ከ20 በመቶ በላይ መሸፈን አልቻለም
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ ከወጪ ንግድ የምታገኘው ገቢ ሸቀጦችን ለማስገባት የምታወጣውን ወጪ ከ20 በመቶ በላይ መሸፈን እንዳልቻለ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ተናግረዋል።
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በወጪና ገቢ ንግዱ ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ነው።
በዚህ ወቅት አሁን ላይ ሀገሪቷ ለወጪ ንግድ ከ15 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ በዓመት ስታወጣ፥ በአንጻሩ ከወጪ ንግድ ከ3 ቢሊየን ዶላር ያልበለጠ ገቢ እንደምታገኝ ተጠቅሷል።
የዘርፉን ችግር በመለየት ቀጣይነት ያለው መፍትሄ ለማስቀመጥም በዘርፉ ከተሰማሩ ባለሃብቶች፣ አምራቾች እና ከሚመለከታችው የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት እየተደረገ ነው ተብሏል።
የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል፥ ውይይቱ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።
በይስማው አደራው
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision