Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የማህበራዊ ድጋፍ መስጠት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የአዕምሮ ጤና፣ የሥነልቡና እና ማህበራዊ ድጋፍ አገልግሎቶችን መስጠት የሚያስችል ስልጠና በሰመራ ከተማ ተጀምሯል፡፡
ስልጠናውን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ፣ የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ከዩኒሴፍ ጋር በመተባብ ነው ያዘጋጁት፡፡
በስልጠናው 900 ለሚሆኑ የጤናና ማህበራዊ ባለሙያዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ታዋቂ ግለሰቦች እና የተለያዩ ተቋማት ተወካዮች እንደሚሰጥ ተመላክቷል፡፡
ስልጠናው በጦርነቱ ምክንያት ለተፈጠሩ ውስብስብ ችግሮች የተቀናጀ ተግባራዊና ዘርፈ ብዙ ምላሽ በመስጠት ዜጎች ከደረሰባቸው ስቃይ እፎይታ እንዲያገኙ ይረዳል ተብሏል፡፡
በተለይም በእውቀት ላይ የተመሰረተ የአዕምሮ ጤና፣ የሥነ ልቡና እና ማህበራዊ ድጋፍ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.