Fana: At a Speed of Life!

በመከላከያ ሠራዊት ስምሪት ዘርፍ ኃላፊ ሜ/ጀ ተስፋዬ አያሌው የተመራ ልዑክ ሶማሊያ በለድዌይን ገባ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ስምሪት ዘርፍ ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት ዋና አስተባባሪ ሜጀር ጀነራል ተስፋዬ አያሌው የተመራ ልዑክ ሶማሊያ በለድዌይን ከተማ ገብቷል፡፡

ልዑካን ቡድኑ የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል መሀመድ አህመድን ጨምሮ፣ የመከላከያ ሠራዊትና የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል አባላትን ያካተተ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሠራዊት አመራር መኮንኖቹ ጉብኝት በጎረቤት ሶማሊያ የሚንቀሳቀሰው አሸባሪው አልሸባብ በአገራችን ድንበር አከባቢዎች ላይ የጀመረውን የሽብር ትንኮሳና ወረራ ለማስቆም ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም በሽብር ቡድኑ ላይ የሚወሰዱ ወታደራዊ እርምጃዎች በሚጠናከሩበትና ቡድኑን ማጥፋት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ ከሶማሊያ መከላከያ ሠራዊትና በሁለቱ ሀገራት አዋሳኝ ላይ የምትገኘውን የሶማሊያ ሂርሸቤሌ ክልል ጸጥታ አመራር ጋር ለመምከር ያለመ መሆኑን ከሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሜ/ጀነራል ተስፋዬ እና ኮሚሽነር ጀነራል መሀመድ አህመድ በቅርቡ አሚሶምን የተካውን በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ተልዕኮ አካል የሆነውና በአካባቢው ከሚገኙ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጋር በሶማሊያና በኢትዮጵያ አዋሳኝ ድንበር ላይ ተደብቀው የሚገኙትን የአሸባሪው አልሸባብ ታጣቂዎች በጋራ ዘመቻ ከአከባቢው ማጽዳትና ማጥፋት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መምከራቸው ተገልጿል።

በድንበር አከባቢ የኢትዮጵያ የሀገር መከላከያና የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ሠራዊት ከሶማሊያ ብሔራዊ ጦርና በሀገራቱ አዋሳኝ አከባቢዎች ሠራዊት ጋር በመተባበር በጥምር ሃይሎቹ አልሸባብን ለመደምስ የተጀመረው የጋራ ዘመቻ ወደ ኢትዮጵያ ሰርገው የሚገቡ የአሸባሪው ቡድን ታጣቂዎችን እንደሚያስወግድ ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.