አሜሪካ በኢራን ይደገፋሉ ባለቻቸው ታጣቂወች ላይ አፀፋዊ እርምጃ ወሰደች
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 4 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በኢራን ይደገፋሉ ባለቻቸው ታጣቂ ቡድኖች ላይ አፀፋዊ እርምጃ መውሰድ መጀመሯ ተነገረ።
ትናንት አንድ የአሜሪካ እና የእንግሊዝ ወታደር እንዲሁም አሜሪካዊ ተቋራጭ በኢራን ይደገፋሉ በተባሉ ታጣቂ ቡድኖች በተፈጸመ የሮኬት ጥቃት መገደላቸው ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም አሜሪካ አምስት የጦር መሳሪያ ማከማቻ ቦታዎችን ኢላማ ያደረገ የአየር ጥቃት መፈጸሟን የሃገሪቱ መከላከያ መስሪያ ቤት አስታውቋል።
ጥቃቱ በኢራን የሚደገፉ ታጣቂዎች ይገለገሉባቸዋል የተባሉ መጋዘኖች መሆናቸውም ነው የተገለጸው።
አሜሪካ በኢራን ይደገፋሉ የምትላቸው ታጣቂዎች ከዚህ ቀደም ለተፈጸሙ 13 ጥቃቶች እጃቸው አለበት በሚል ትወቅሳለች።
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision