የጤና ሚኒስቴር፣ የክልሎችና ተጠሪ ተቋማት የጋራ ኮሚቴ የኮሮና ቫይረስ ቅድመ መከላከል ስራዎችን ገመገመ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጤና ሚኒስቴር፣ የክልሎችና ተጠሪ ተቋማት የጋራ ኮሚቴ በኮሮና ቫይረስ ቅድመ መከላከል ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን ገመገመ።
የጤና ሚኒስቴር፣ የክልሎችና ተጠሪ ተቋማት የጋራ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ሲያደርግ የቆየውን ስብሰባ አጠናቋል።
በስብሰባው ላይም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና ሚኒስትር ደኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማን ጨምሮ የክልል የጤና ቢሮዎች እና ተጠሪ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።
ከመጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ላለፉት ሁለት ተከታታይ ቀና የተካሄደው ስብሰባውም በኮሮና ቫይረስ ቅድመ መከላከል ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን መገምገሙን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
እንዲሁም በሌሎች አጀንዳዎችም ላይ ውይይት በማካሄድ እና በቀጣይ መሰራት ስለሚገባቸው ተግባራት አቅጣጫ በማስቀመጥ ስብሰባውን አጠናቋል።