Fana: At a Speed of Life!

ወጣቶች በመዲናዋ የተከናወኑ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ 1 ሺህ 200 ወጣቶች በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ስራዎችንና የተለያዩ ተቋማትን እየጎበኙ ነው፡፡

በጉብኝታቸውም የአብርሆት ቤተ መጻሕፍትን፣ ሳይንስ ሙዝዬምን፣ አንድነት እና ወንድማማችነት ፓርክን እንዲሁም የቤተ-መንግስት ፓርኪንግ አገልግሎትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡

ወጣቶች÷ የጉብኝት መርሐ ግብሩ ልምዶችን በመቅሰም በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች መሰል የልማት ስራዎችን ለማስፋት እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማና በፌዴራል መንግስት ስር የሚገኙ ተቋማትን እየጎበኙ ሲሆን÷ ይህም እንደ ሀገር እየተከናወኑ የሚገኙ ተቋማዊ እንቅስቃሴዎችን ለመገንዘብ ይረዳቸዋል ተብሏል፡፡

ውይይቱ “የኔ ዘመን ወጣት ሚና” በሚል በሪ ሃሳብ በሁሉም አካባቢዎች ሲደረግ የነበረውን የወጣቶች ውይይት በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማጠቃለል ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም የኢትዮጵያን የወደፊት እድል በመወሰን ወጣቱ የሚኖረውን ሚና ለማመላከት ያለመ ነው መባሉን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ሀገር አቀፍ የወጣቶች የጉብኝት መርሐ ግብሩ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን÷ ነሐሴ 15 ቀን 2014 የማጠቃለያ ውይይት እንደሚኖር ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.