Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የትምህርት ጉባዔ መካሔድ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 24ኛው የትምህርት ጉባዔ እና ክልል አቀፍ የትምህርት ንቅናቄ በአሶሳ ከተማ መካሔድ ጀምሯል፡፡

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጉባዔ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰንን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት፣ መምህራንና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ነው፡፡

በጉባዔው የ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘርፍ አፈጻጸም ላይ ውይይት እንደሚካሄድ እና በዘርፉ ላጋጠሙ ችግሮች የመፍትሔ ሃሳቦች እንደሚቀመጡ ተመላክቷል፡፡

በክልሉ በነበረው የጸጥታ ችግር የተዘጉ ትምህርት ቤቶች እንደሚከፈቱና የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለማቋቋም ህብረተሰቡን ያሳተፈ ስራ ይሰራል መባሉን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ሕጻናትን ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ የሚያስችል የንቅናቄ ሠነድም ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሏል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.