Fana: At a Speed of Life!

የሲቪል ማህበራትና የፖለቲካ ፓርቲ ምክር ቤቶች በሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት ላይ እየመከሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት ላይ የበኩላቸውን መወጣት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ እየመከሩ ነው።

በውይይቱ ላይ ሁለቱ ምክር ቤቶች በሀገራዊ ጥቅም ላይ በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸው ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ሄኖክ መለስ ÷የሀገራዊ ምክክሩ ዋና ዓላማ ሀገራዊ መግባባትን መፍጠር በመሆኑ ሁለቱም ምክር ቤቶች ለስኬታማነቱ የበኩላቸውን ይወጣሉ ብለዋል።

የሀገራዊ ምክክር ሂደትም አሳታፊ፣ ግልጽ እና ነጻ እንዲሆን የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡም ጠቁመዋል።

የፖለቲካ ፖርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዶክተር ራሄል ባፌ በበኩላቸው÷ ሁለቱ ምክር ቤቶች ለሀገር ጠቀሜታ ባላቸው ጉዳዮች ላይ ያደረጉት ጥምረት ዘላቂ እንዲሆን ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል።

ሀገራዊ ምክክሩም የታለመለትን ግብ እንዲመታ ምክር ቤቱ የሚጠበቅበትን ለመወጣት ይሰራል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በውይይቱ በብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማኅበራት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ዓለሙ ስሜ፣ የሁለቱ ምክር ቤቶች ተወካዮች፣ የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.