የአፋር ክልል ማዕድን ልማት ኮርፖሬሽን ስራ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በግማሽ ቢሊየን ብር መነሻ ካፒታል የተቋቋመው የአፋር ክልል ማዕድን ልማት ኮርፖሬሽን ዛሬ በይፋ ስራ ጀመረ፡፡
ኮርፖሬሽኑ አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ወደ ስራ መግባቱ ተገልጿል።
ስትራቴጂካዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቃሜታ ያላቸውን የክልሉ የማዕድን ሀብቶች በጥናት በመለየትና በማልማት የሕብረተሰቡን ኑሮ በማሻሻል የክልሉንና የኢትዮጵያን መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ መደገፍ ዋነኛ ተልዕኮው ነው ተብሏል።
ኮርፖሬሽኑ በማዕድን ግብይቱ ውስጥ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ሀገር አቀፍና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ተቋም መገንባት አላማ አድርጎ እንደሚንቀሳቀስ የአፋር ክልል መንግስት መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል ።
የክልሉ መንግስት ለኮርፖሬሽኑ ስራ ስኬታማነት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቋል።