Fana: At a Speed of Life!

1ሺህ 29 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 29 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

ለተመላሽ ዜጎች ተገቢው ድጋፍ እና እንክብካቤ ተደርጎላቸው ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማዕከላት መሄዳቸው ተገልጿል፡፡

ዛሬ በሦስት ዙር ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው 1 ሺህ 29 ዜጎች መመለሳቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

እስካሁን ድረስ በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ሥራ 69 ሺህ 683 ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.