በወልዲያ ከተማ በ138 ሚሊየን ብር የተገነባው የአስተዳደር ሕንጻ ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ይልቃል ከፋለ በወልዲያ ከተማ የተገነባውን ባለ 6 ወለል የከተማ አስተዳደር ሕንጻ መረቁ፡፡
ለግንባታው 138 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን ገንዘቡም በከተማ አስተዳደሩ መሸፈኑ ተመላክቷል፡፡
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ እንደተገለጸው÷ ወልዲያ ከተማ ወደ ሪጂኦፖሊታንት ከተማ ማደጓን ተከትሎ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመሥጠት እንዲቻል መሰል ፕሮጀክቶች ያስፈልጋሉ፡፡
የወልዲያ ከተማ አሁን ካለችበት ከፈርጂ አንድ ወደ ሪጂዮፖሊታንት ደረጃ ሽግግር ስነ ስርዓት እየተካሄደ ነው፡፡
በታሪኩ ለገሰ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!