Fana: At a Speed of Life!

ጀርመን የኃይል ቁጠባ ዕቅዱን አጸደቀች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጀርመን በጋዝ አጠቃቀም ላይ ገደብ የሚጥለውን የኃይል ቁጠባ ዕቅድ ማጽደቋን አስታወቀች።

የፀደቀው የኃይል ቁጠባ ዕቅድ ቢሮዎች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚጠቀሙትን የሙቀት መጠን ከ19 እስከ 20 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ባለው እንዲሆን የሚገድብ ነው ተብሏል፡፡

ትናንት የጀርመን ካቢኔ አባላት ከተሰበሰቡ በኋላ የሀገሪቷ የኢኮኖሚ ሚኒስትር ሮበርት ሀቤክ በበርሊን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ሮበርት ሀቤክ በሠጡት መግለጫ ÷ የጀርመን መንግስት በሀገሪቷ በሚኖረው ቀጣይ የሙቀት ወቅት የጋዝ አጠቃቀምን ለመቀነስ ይረዳው ዘንድ የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰድ የሚያስችሉ ጥቅል ዕቅዶች ማጽደቁን ተናግረዋል፡፡

በጸደቀው ዕቅድ መሠረትም ÷ የምሽት የውጭ ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ፣ የመጋዘን በረንዳ መብራቶች በየቀኑ ከምሽቱ 4 ሠዓት ጀምሮ እስከ ንጋት 12 ሠዓት ድረስ ለስምንት ሠዓታት ጠፍተው እንዲቆዩ ተወስኗል ብለዋል፡፡

ውሳኔው ከፈረንጆቹ መስከረም 1 ቀን ጀምሮ ቀስ በቀስ እስከ ጥቅምት ባለው ጊዜ እንደሚተገበር ተነግሯል፡፡

በጸደቀው ዕቅድ መሠረት ጀርመናውያን የጋዝ አጠቃቀማቸውን ከ2 እስከ 2 ነጥብ 5 በመቶ ይቀንሳሉ ነው የተባለው፡፡

የትግበራ እርምጃው እንደ ጤና ተቋማት እና ሆስፒታል ያሉ የማኅበረሰብ አገልግሎት ሠጪ ተቋማትን እንደማይመለከትም አር ቲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.