በደቡብ ክልል በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል በወቅታዊ ክልላዊና ሀገራዊ የፀጥታ ሁኔታና ሕግ ማስከበር ጉዳዮች ላይ የሚመክር መድረክ በሐዋሳ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ ላይ ከክልል ማዕክል፣ ከዞን፣ ልዩ ወረዳና ከተማ አስተዳደር የፀጥታ መዋቅር አመራሮች እየተሳተፉ መሆኑን የኢዜአ ዘገባ ጠቁሟል።
ወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ የፀጥታ ነባራዊ ሁኔታን መነሻ በማድረግ በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት እንደሚደረግም ነው የተጠቆመው።
በዚህም የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አለማየሁ ባውዲ ባደረጉት ንግግር፥ የፀጥታ ተቋማት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በመፍጠር ሁለንተናዊ የሆነ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ክልሉ መሰናዳቱን ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-