Fana: At a Speed of Life!

የተመድ ረዳት ዋና ፀሃፊ ህወሓት በመቀሌ የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን ላይ የፈፀመው ዝርፊያ እንደረበሻቸው ገለፁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ፀሃፊና የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትዝ፥ ህወሓት በመቀሌ የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን ላይ የፈፀመው ዝርፊያ እንደረበሻቸው ገለፁ።

ረዳት ዋና ፀሃፊው በጉዳዩ ላይ መግለጫ አውጥተዋል።

በመግለጫቸውም ህወሓት የዘረፈው 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ፥ ተመድ እና አጋር ድርጅቶች ድጋፍ ለሚሹ የክልሉ ዜጎች የሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ የሚጠቀሙበት ነበር ብለዋል።

ነዳጅ ከሌለ ተረጂዎች ምግብ፣ አልሚ ንጥረ ነገር፣ መድሐኒት እና ሌሎች ጠቃሚ አቅርቦቶችን ማግኘት እንደማይችሉ ማርቲን ግሪፊትዝ ጠቁመዋል፡፡

የተመጣጠነ ምግብ እጥረትና የምግብ አቅርቦት ችግር ባለበት በዚህ ወቅት፥ እንዲህ ዓይነት ዝርፊያ የከፋ ሁኔታ እንደሚፈጥር ነው ያስጠነቀቁት።

ማንኛውም የእርዳታ ቁሳቁስን በዚህ መልኩ ለሌላ ተግባር ማዞርን አጥብቀው እንደሚያወግዙ ረዳት ዋና ፀሃፊው አስታውቀዋል።

የረድኤት አቅርቦቶች መጠበቅ አለባቸው ያሉት ማርቲን ግሪፊትዝ ፥ የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ስርጭትን ማስተጓጎል መቆም አለበት ብለዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.