አሸባሪው ህወሓት ጦርነት በከፈተበት ግንባር ነዳጅ ጭኖ ሊገባ የነበረ ተሽከርካሪ ተያዘ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት ጦርነት በከፈተበት ግንባር ናፍታ እና ቤንዚን ሊያቀብል የነበረ “አይሱዙ” የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ መያዙን መከላከያ ሰራዊት አስታወቀ፡፡
መነሻውን ሠመራ ከተማ ያደረገው ተሽከርካሪ÷ መዳረሻውን ወደ አሸባሪው ህወሓት ቡድን በማድረግ 3 ሺህ ሊትር ናፍታ እና 2 ሺህ ሊትር ቤንዚን ጭኖ ሲጓዝ ካልዋን ላይ መያዙን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!