የህወሓትን ወረራ ለመከላከል የሚደረገውን ተጋድሎ እንደሚደግፉ የደቡብ አፍሪካ ዳያስፖራዎች ገለጹ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሸባሪውን ህወሓት ወረራ ለመከላከል የሚደረገውን ተጋድሎ እንደሚደግፉ በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት ተናገሩ፡፡
በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ፥ የኢትዮጵያ የዳያስፖራ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ፣ ዲጅታል ዲፕሎማሲ፣ የሚዲያ አካላት እና ሌሎች የማህበረሰቡ አደረጃጀቶች የተሳተፉበት ውይይት ተካሂዷል፡፡
በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሙክታር ከድር÷ መንግሥት ግጭቱን በሰላማዊ መንግድ ለመፍታት የሰላማዊ ውይይት ኮሚቴ በማቋቋም ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት ማረጋገጡን አብራርተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የዳያስፖራ አደረጃጀት አባላት በበኩላቸው÷ በአገር ሉዓላዊነት እና በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ የሚሰነዘሩ ማናቸውም አደጋዎች ፈጽሞ ተቀባይነት የሌላቸውና ለድርድር የማይቀርቡ መሆናቸውን አንስተዋል።
አሸባሪው ህወሓት ሁሉንም የሰላም አማራጮች በመርገጥ የፈጸመው ዳግም የጦርነት ዘመቻ የቡድኑን አገር የማፍረስ እኩይ ዓላማ በገሃድ ያረጋጋጠ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
በደቡባዊ አፍሪካ የሚገኙ የዳያስፖራ አባላት፥ የህልውና አደጋውን ለመቀልበስ የተጀመረውን ርብርብ እንዲቀላቀሉ ለማደረግ ሰፊ እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!