ጠላት የቱንም ያህል ቢፎክር ድል ማስመዝገብ የሚችል አስተማማኝ ኃይል ፈጥረናል-በግዳጅ ቀጠና የሚገኙ የዕዝ ዋና አዛዥ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊ ጀግንነታችን ምንጊዜም የማይነጥፍ ነው ሲሉ በግዳጅ ቀጠና የሚገኙ አንድ የዕዝ ዋና አዛዥ ተናገሩ።
የጀግኖች ሀገር ኢትዮጵያ ተሸንፋም ተንበርክካም አታውቅም ያሉት የዕዙ ዋና አዛዥ፥ በእኛም ዘመን ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ትከበራለች እንጂ አትደፈርም ብለዋል።
ጠላት የቱንም ያህል ቢፎክር በሥነ ልቦናም ይሁን በማቴሪያል ዝግጁነታችንን አጠናክረን ትናንት የፈጸምነውን ገድልና ጀግንነት ማስቀጠልና ድል ማስመዝገብ የሚችል አስተማማኝ ኃይል ፈጥረናል ሲሉም ተናግረዋል።
አክለውም የውጭ ጠላቶች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመዳፈር እና ህዝቦቿን ለማሰቃየት ሁሌም ይጥራሉ፥ ነገር ግን አይሳካላቸውም ነው ያሉት፡፡
ኢትዮጵያን ነክቶ በሰላም የተኛ እንደሌለ የገለጹት የዕዙ ዋና አዛዡ÷ ጠላቶቻችን እስኪጸጸቱ ድረስ በለኮሱት እሳት ወደ አመድነት የሚቀይራቸው የመከላከያ ኃይል አፍርተናል ማለታቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!