በናይጄሪያ በጋዝ ማስተላለፊያ መስመር ላይ በደረሰ ፍንዳታ የ17 ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በናይጄሪያ በጋዝ ማስተላለፊያ መስመር ላይ በደረሰ ፍንዳታ የ17 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተነገረ።
ፍንዳታው ከባድ የጭነት ተሽከርካሪ በነዳጅ ማውጫ ስፍራ የሚገኙ የጋዝ ሲሊንደሮችን ከገጨ በኋላ የተፈጠረ መሆኑ ተገልጿል።
በአደጋው ሳቢያ ከሞቱት በተጨማሪም በአካባቢው የሚገኙ ከ100 በላይ መኖሪያ ቤቶችን ጨምሮ የንግድ ሱቆች ወድመዋል።
በተጨማሪም በፍንዳታው የተለያዩ ተሽከርካሪወች ወድመዋል ነው የተባለው።
ባለፈው ሃምሌ ወር ላይ በነዳጅ ጫኝ ቦቴ ላይ በተከሰተ ፍንዳታ 45 ሰዎች ሲሞቱ ከ100 በላይ የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸው የሚታወስ ነው።
ምንጭ፦ አልጀዚራ