Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በቤት ልማት ፋይናንስ አቅርቦት ዙሪያ ከፋይናንስ ተቋማት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ በቤት ልማት ፋይናንስ አቅርቦት ዙሪያ ከከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችና የፋይናንስ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ እዮብ ተካልኝን ጨምሮ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ምክትል ፕሬዚዳንትና የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡

በውይይቱ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅዱን ማዕከል በማድረግ የተቀረጹ የቤት ልማት አማራጮችን ዕውን ለማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንዲሁም የፋይናንስ ችግሩን ለመቅረፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

ወደፊትም በጋራ አብሮ ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጎ መግባባት ላይ መደረሱን ከከተማና መሰረተ-ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.